Pair of Vintage Old School Fru
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ኢስላማዊ ጥያቄና መልስ ክፍል 2


QandA

1 የኸድጃ(ረ.ዐ) ሴት ልጅ ከባሏ ኡስማን ኢብን አፋን ጋር ወደ አቢሲንያ (ኢትዮጽያ) የተሰደደችው_______ነበረች?

ሀ) ፋጢማ

ለ) ዘይነብ

ሐ) ሩቅያ

መ) ኡሙ ኩልሱም

2 ኸሊሉሏህ በመባል የሚታወቀው ማን ነው?

ሀ) ኢሳ(ዐ.ሰ)

ለ) ኢብራሊም(ዐ.ሰ)

ሐ) ኢስማኤል(ዐ.ሰ)

መ) ኢድሪስ(ዐ.ሰ)

3 ኑህ(ዐ.ሰ) ቢያንስ ለ______ዓመታት ያህል ኑሯል?

ሀ) 775

ለ) 885

ሐ) 950

መ) 980

4 አደም(ዐ.ሰ) እና ሐዋ(ዐ.ሰ) በመጀመሪያ ይኖሩ የነበረው የት ነው?

ሀ) በምድር

ለ) ሰማይ

ሐ) ጀሃነም

መ) ጀነት

5 አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ለመላዒካዎች ከሸክላ(አፈር)________ልፈጥርነው አላቸው?

ሀ) እንሰሳ

ለ) ጅን

ሐ) በሸር

መ) መልሱ የለም

6 አኢሻ(ረ.ዐ)_______ያህል ሐዲሶችን ዘግባለች?

ሀ) 1730

ለ) 2210

ሐ) 3420

መ) 4140

7 የአኢሻ(ረ.ዐ) የታለቅ እህቷ ስም________ነበር?

ሀ) ሰልማ(ረ.ዐ)

ለ) ዘይነብ(ረ.ዐ)

ሐ) አስማ(ረ.ዐ)

መ) ሐፍሳ(ረ.ዐ)

8 የአኢሻ(ረ.ዐ) አባት________ነበር?

ሀ) አቡ-ጧሊብ(ረ.ዐ)

ለ) ኡስማን(ረ.ዐ)

ሐ) አቡ በክር(ረ.ዐ)

መ) ኡመር(ረ.ዐ)

9 ፋጢማ(ረ.ዐ) እና ባሏ አምስት ልጆች ነበሯቸው። ሐሰን ፣ ሁሴን ፣ ዘይነብ ፣ ኡሙኩልሱም እና_______

ሀ) ሙህሲን

ለ) ቃሲም

ሐ) አብዱሏህ

መ) ኢብራሂም

10 በአሊ(ረ.ዐ) እና በፋጢማ(ረ.ዐ) የሰርግ በዓል እለት የተገኙ እንግዶች የተስተናገዱት______ነበር?

ሀ) በበግስጋ በደረቅ ፍራፍሬ

ለ) በዶሮ ወጥ

ሐ) በተምርና ከማር በተሰራ መጠጥ

መ) በጥብስና በሻይ

11 አብዱ-ረህማን በበድር ጦርነት ወቅት ከኩፋሮች ጋ ሆኖ ሲዋጋ የነበረው የ______ልጅ ነው?

ሀ) ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)

ለ) ኡመር(ረ.ዐ)

ሐ) ኡስማን(ረ.ዐ)

መ) አቡበክር(ረ.ዐ)

12 ከኡመር(ረ.ዐ) ጠቃሚ ምክሮች ውስጥ አንዱ_______ነው?

ሀ) እንከኖችህን የሚያወጣልህን የሚነግርህን ሰው አመስግን

ለ) ሁልጊዜም ሶላትን በወቅቱ ስገድ

ሐ) መጥፎ ነገርን ታገል

መ) ለእውነት ቁም

13 በአሏህ(ሱ.ወ) ትእዛዝ መሠረት ነብዩ ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ልጃቸውን________መስዋዕት ሊያደርጉ ዝግጁ ነበሩ?

ሀ) ኢስሐቅ

ለ) ኢስማኢል

ሐ) ኢድሪስ

መ) ኢልያስ

14 በላቸው እናንተ ከሐዲዎች ሆይ! በማለት የሚጀምረው የቁርአን ሱራ የትኛው ነው?

ሀ) አል-ናስር

ለ) አል-አስር

ሐ) አል-ካፊሩን

መ) አል-በቀራ

15 አቡ-በክር(ረ.ዐ) ካበረከቷቸው ነገሮች መካከል አንዱ______ነበር?

ሀ) ገንዘብ መሠብሰብ

ለ) ብዙ መስጅዶችን መገንባት

ሐ) ግብፅን በሸሪአ ህግ ማስተዳደር

መ) መልሱ የለም

16 አሊ(ረ.ዐ) በበድር በ_____እና በ_____ጦርነቶች ተሳትፏል?

ሀ) ኸይበር፤ ኡኹድ

ለ) አኽዛብ፤ ኸይበር

ሐ) አኽዛብና ኡኹድ

መ) መልስ የለም

17 ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከአለም ሴቶች መካከል 4 ሴቶች ታላቆች ናቸው ብለዋል። ኸድጃ ፣ ፋጢማ ፣ መርየም እና_____

ሀ) አኢሻ(ረ.ዐ)

ለ) አስማ(ረ.ዐ)

ሐ) አሲያ(ረ.ዐ)

መ) ሰውዳ(ረ.ዐ)

18 ሱራ አል-አስርን መሠረት በማድረግ የሰው ልጅ በእጦት(በኪሳራ) ላይ ናቸው። እነዛ_______ሲቀሩ?

ሀ) ያመኑ

ለ) መልካም ስራ የሰሩ

ሐ) በሐቅና በትዕግስት አደራ የተባባሉት

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

19 በጥንት ጊዜ የግብፅ ኑጉሶች______በመባል ይታወቁ ነበር?

ሀ) ቡራቅ

ለ) ሲዛር

ሐ) ፊርአውን

መ) ኸሊፋ

20 ሐታ ዘርቱሙል መቃቢር ማለት______ማለት ነው?

ሀ) ጌታችሁን አልቁት

ለ) ለጌታችሁም ስገዱ፤ እርሱንም ብቻ ለምኑ።

ሐ) በእርግጥ የሰው ልጆች በኪሳራ ውስጥ ናቸው

መ) መቃብራችሁን እስክት ጐበኙ ድረስ

21 መልካም ስራን በሰራን ጊዜ______መጠበቅ አለብን?

ሀ) የሰዎችን ምስጋና እና አድናቆት

ለ) ከሰዎች ገንዘብ

ሐ) የአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ምንዳ

መ) ሁሉም መልስ ናቸው

22 አሏህ በጊዜ እየማለ የሚጀምርበት ሱራ______ነው?

ሀ) አል-በቀራ

ለ) አጢን

ሐ) ሙዘሚል

መ) አል-አስር

23 ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) እስቲግፋር የጠየቁበት ሱራ የትኛው ነው?

ሀ) አል-ካፊሩን

ለ) አል-ጢን

ሐ) አል-ፊል

መ) አል-ነስር

24 የአል-ጢን ትርጉም______ነው?

ሀ) የወይራ ዛፍ

ለ) የበለስ ዛፍ

ሐ) ጊዜ

መ) ሰዎች

25 የነስር ትርጉሙ______ነው?

ሀ) ድል

ለ) ቅጣት

ሐ) ምንዳ

መ) ምህረት

26 የአቡ-በክር(ረ.ዐ) ሌላኛ መጠሪያ ምን ነበር?

ሀ) አበል ቃሲም

ለ) አል-ፋሩቅ

ሐ) አሳዱሏህ

መ) አሲዲቅ

27 የነብዩ ሙሷ(ዐ.ሰ) ወንድም______ነው?

ሀ) ሐሩን

ለ) ሐማን

ሐ) ኢምራን

መ) ዳውድ

28 ኸድጃ(ረ.ዐ) ነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) ስታገባ እድሜዋ ስንት ነበር?

ሀ) 30 ዓመት

ለ) 40 ዓመት

ሐ) 50 ዓመት

መ) 60 ዓመት

29 ጣኦታቶችን ሰባብሮ መጥረቢያውን ከትልቁ ጣኦት ላይ አንጠልጥሎ የሄደው ማነው?

ሀ) ሙሳ(ዐ.ሰ)

ለ) ኢብራሂም(ዐ.ሰ)

ሐ) ኑህ(ዐ.ሰ)

መ) ኢሳ(ዐ.ሰ)

30 የነብዩ ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ቅፅል ስም ምን ነበር?

ሀ) ኸሊሉሏህ

ለ) አሳዱሏህ

ሐ) ረሱሉሏህ

መ) መልሱ የለም

31 በኡኹድ ጦርነት የተሳተፈችና የቆሰሉ ሙስሊም ወታደሮችን ስታክም የነበረች______ናት?

ሀ) አኢሻ(ረ.ዐ)

ለ) ፋጢማ(ረ.ዐ)

ሐ) ሐፍሳ(ረ.ዐ)

መ) ሱመያ(ረ.ዐ)

32 ሰይደቱን ኒሳእ በመባል የምትጠራው ማንናት?

ሀ) ሰውዳ(ረ.ዐ)

ለ) አኢሻ(ረ.ዐ)

ሐ) ሐፍሳ(ረ.ዐ)

መ) ፋጢማ(ረ.ዐ)

33 ባንድ ወቅት የሙስሊም ወታደሮች አዛዥ የነበረ ቡኻላ ላይ ግን ተራ ወታደር የሆነ ማንነው?

ሀ) ሐሊድ ቢን ወሊድ

ለ) አቢ ኡበይዳ

ሐ) ሰአድ ቢን አቢወቃስ

መ) መልሱ የለም

34 ከአራቶቹ አማራጮች መካከል ተሰጥኦ ያለው ተናጋሪ ማንነበር?

ሀ) ኡመር(ረ.ዐ)

ለ) አቡ-በክር(ረ.ዐ)

ሐ) ኡስማን(ረ.ዐ)

መ) አሊ(ረ.ዐ)

35 አልፋሩቅ ማለት______ነው?

36 አቡ-በክር(ረ.ዐ) ኸሊፋ ሁነው የገዙት ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ሀ) 4 ዓመት 9 ወር

ለ) 12 ዓመት

ሐ) 10 ዓመት 6 ወር ከ4 ቀን

መ) 2 ዓመት ከ3 ወር

37 በኡኹድ ጦርነት ሐምዛን(ረ.ዐ) የገደለው ማንነው?

ሀ) አዶልፍ ሂትለር

ለ) ዋህሺ

ሐ) አቡላሃብ

መ) መልሱ የለም

38 ኸሊፋ ኡመር(ረ.ዐ) ለምን ያህል ጊዜ ነው ያስተዳደሩት?

ሀ) ከ10 ዓመት በላይ

ለ) ከ10 ዓመት በታች

ሐ) 2 ዓመት
ከ6 ወር

መ) 7 ዓመት ከ8 ወር ከ45 ቀን

39 ለምን ያህል ጊዜ ነው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዳዕዋ ያደረጉት?

40 ሐጅን ተከትሎ የሚመጣ ኢድ_____ነው?

ሀ) ኢዱል አዱሐ

ለ) ኢዱል ፊጥር

ሐ) አቂቃ

መ) ወሊማ


9546

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ